አንቀጾቹ ቁርኣን ግልጽ መጽሐፍ በመሆኑ ታላቅነቱን ያበራራሉ። ለምእመናን መሪያና ፈውስ ሲሆን፣ ለማያምኑት ግን ከሩቅ ቦታ እንደሚጠሩ ያህል መስማት አለመቻልና ዕውርነት እንደሆነ ያብራራሉ። አንቀጾቹ በዘላለማዊው የአላህ ፍትህ ህግ ይጠናቀቃሉ፦ መልካም የሰራ ለራሱ ነው፣ ክፉም የሰራ በራሱ ላይ ነው፤ አላህም በባሪያዎቹ ላይ በዳይ አይደለም።