እነዚህ አንቀጾች ሰይጣን በትዕቢት ለመስገድ እንቢ ካለበት ጊዜ ጀምሮ በሱ እና በአዳም ልጆች መካከል ያለውን የታሪክ ጠላትነት የሚያስታውሱ ሲሆን፡ ሰዎችን እሱንና ዘሮቹን ከአላህ ውጭ ረዳት አድርገው ከመያዝ ያስጠነቅቃሉ። በትንሣኤ ቀን የሐሰት አማልክትን አቅም ማጣት በማሳየት የሽርክን ውድቅነት ያረጋግጣሉ፤ አላህ ሰዎች እንዲያስቡበት በቁርዓን ውስጥ የተለያዩ ምሳሌዎችን ማብራራቱን ያጎላሉ። የአላህ መልእክተኞች ተግባር ብስራትን ማበሰር እና ከማስተባበል ውጤት ማስጠንቀቅ መሆኑን ያብራራሉ። በመጨረሻም፡ የፊተኞቹ ህዝቦች መጥፋት የበደል ውጤት እንጂ የአላህ ግፍ እንዳልሆነ፡ ይህም ግልጽ ማስረጃዎች ከበቁአቸው በኋላ በተወሰነው ጊዜ የተከሰተ መሆኑን ያረጋግጣሉ።